The Noble Qur'an Encyclopedia
Towards providing reliable exegeses and translations of the meanings of the Noble Qur'an in the world languagesThe Opening [Al-Fatiha] - Amharic translation - Africa Academy
Surah The Opening [Al-Fatiha] Ayah 7 Location Maccah Number 1
1. በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው (እጀምራለሁ)::
2. ምስጋና ሁሉ ለዓለማቱ ጌታ ለአሏህ ይገባው።
3. እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ ለሆነው::
4. የፍርዱ ቀን ባለቤት ለሆነው (ለአላህ ብቻ ይገባው)::
5. (ሙስሊሞች ሆይ! ጌታችሁን) አንተን ብቻ እንገዛለን:: ካንተም ብቻ እርዳታን እንለምናለን (በሉ)።
6. ቀጥተኛውን መንገድ ምራን::
7. የእነዚያን ለእነርሱ በጎ የዋልክላቸውን፤ በእነርሱ ላይ ያልተቆጣህባቸውንና ያልተሳሳቱትንም ሰዎች መንገድ (ምራን በሉ)::