عربيEnglish

The Noble Qur'an Encyclopedia

Towards providing reliable exegeses and translations of the meanings of the Noble Qur'an in the world languages

Competition [At-Takathur] - Amharic Translation - Africa Academy

Surah Competition [At-Takathur] Ayah 8 Location Maccah Number 102

(በዚህች ዓለም ጸጋዎች) ብዛት መፎካከር (ጌታችሁን ከመገዛት) አዘናጋችሁ።

መቃብሮችን እስከጎበኛችሁ ድረስ። (በዚሁ ላይ ቀጠላችሁ)።

ከዚህ ተግባራችሁ ተከልከሉ (ታቀቡ)። ወደፊት (ውጤቱን) ታውቃላችሁ፤

ከዚያም ከዚህ ተግባራችሁ ተከልከሉ። ወደ ፊትም ታውቃላችሁ፤

በእውነቱ (የሚጠብቃችሁን) በእርግጠኝነት ብታውቁ ኖሮ (ይህን ያክል ባልተዘናጋችሁ ነበር)።

ገሀነምን በእርግጥ ታያላችሁ።

ከዚያም እርግጠኛን ማየት ታዩዋታላችሁ፤

ከዚያም በድሎታችሁ ጉዳይ ሁሉ በዚያ ቀን ትጠየቃለችሁ።