عربيEnglish

The Noble Qur'an Encyclopedia

Towards providing reliable exegeses and translations of the meanings of the Noble Qur'an in the world languages

The victory [Al-Fath] - Amharic Translation - Africa Academy

Surah The victory [Al-Fath] Ayah 29 Location Madanah Number 48

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እኛ ላንተ ግልጽ የሆነን ድል ከፈትንልህ (ለገስንህ።)

አላህ ያለፈውንና የሚመጣውን ኃጢአትህን ሊምርህ፤ ፀጋውንም ባንተ ላይ ሊሞላና ቀጥተኛዉን መንገድ ሊመራህ፤

አላህም ብርቱን እርዳታ ሊረዳህ (ከፈተልህ።)

አላህ ያ በአማኞች ልቦች ውስጥ ከእምነታቸው ጋር እምነትን ይጨምሩ ዘንድ እርጋታን ያወረደ ነው። አላህ የሰማያትና የምድር ሰራዊት ሁሉ የሱ ብቻ ነው። አላህ ሁሉን አዋቂና ጥበበኛ ነው።

ወንድ አማኞችና ሴት ምዕመናትን በስሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች በውስጣቸው ዘወታሪዎች ሲሆኑ ሊያስገባቸው፤ ከነርሱም ሐጢያቶቻቸዉን ሊያብስላቸው (ይህንን አደረገ)። ይህም ከአላህ ዘንድ የሆነ ታላቅ መታደል ነው።

ወንድ አስመሳዮችንና ሴት አስመሳዮችን፣ ወንድ አጋሪዎችንና ሴት አጋሪዎችን፣ እነዚያን በአላህ ክፉ ጥርጣሬን ተጠራጣሪዎች የሆኑትን ያሰቃይም ዘንድ (ይህንን አደረገ)። በእነርሱ ላይ ክፉ ከባቢ አለባቸው። በእነርሱ ላይ አላህ ተቆጣባቸው ረገማቸዉም። ለእነርሱ ገሀነምን አዘጋጀላቸው። ገሀነም መመለሻነቷም ከፋች።

ለአላህ የሰማያትና የምድር ሰራዊቶች አሉት። አላህ ሁሉን አሸናፊና ጥበበኛ ነው።

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እኛ መስካሪ፤ አብሳሪና አስፈራሪ አድርገን በእርግጥ ላክንህ።

በአላህ ልታምኑ። በመልዕክተኛዉም ልታምኑ፤ ልትረዱትና ልታከብሩት፤ አላህንም በጠዋትና ከቀትር በኋላ ልታወድሱት (ላክንህ)።

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያ ቃል ኪዳን የሚጋቡህ ቃል ኪዳን የሚጋቡት አላህን ብቻ ነው። የአላህ እጅ ከእጆቻቸው በላይ ነው። ያፈረሰም ሰው የሚያፈርሰው በነፍሱ ላይ ብቻ ነው። በእርሱ ላይ አላህን ቃል ኪዳን የተጋባበትን የሞላ ሰው ታላቅ ምንዳ በእርግጥ ይሰጠዋል።

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከዐረብ ዘላኖች መካከል እነዚያ ከዘመቻ ወደ ኋላ የቀሩት «ገንዘቦቻችንና ቤተሰቦቻችን አስቸግረዉን ስለነበር ነውና (የቀረነው) ምህረትን ለምንልን» ይሉሃል። በልቦቻቸው ውስጥ የሌለውን ነገር በምላሶቻቸው ይናገራሉ። «አላህ እናንተን መጉዳትም ሆነ መጥቀም ቢፈልግ ከአላህ ለእናንተ አንዳችን ለመከላከል የሚችል ማን ነው? በእውነቱ አላህ ለምትሰሩት ነገር ሁሉ ውስጠ አዋቂ ነው።» በላቸው።

ይልቁንም መልዕክተኛውና ምዕመናኖቹ ወደየቤተሰቦቻቸው ፈጽሞ አይመለሱም ብላችሁ ስለጠረጠራችሁ ነው። ይህም በልቦቻችሁ ውስጥ ተሸለመላችሁ። መጥፎንም መጠርጠር ጠረጠራችሁ ጠፊዎች ህዝቦችም ሆናችሁ።

በአላህና በመልዕክተኛው ያላመነ ሰው (ከሓዲ ነው)፤ እኛ ለከሓዲያን እሳትን አዘጋጅተናል።

የሰማያትና የምድር ንግስና የአላህ ብቻ ነው። ለሚፈልገው ሰው ይምራል። የሚፈልገውንም ሰው ይቀጣል። አላህ መሀሪና አዛኝ ነውና።

ከጠላት የተማረኩትን ገንዘቦች ልትይዙ በሄዳችሁ ጊዜ እነዚያ ወደ ኋላ የቀሩት ሰዎች «ተውን እንከተላችሁ» ይሏችኋል። በዚህም የአላህን ቃል ሊለውጡ ይፈልጋሉ። «ፈጽሞ አትከተሉንም። ልክ እንደዚሁ አላህ ከዚህ በፊት ብሏል» በሏቸው። «ይልቁንም ትመቀኙናላችሁ» ይላሉም። በእውነት እነርሱም ጥቂትን እንጂ የማያውቁ ነበሩ።

ዘላኖች (ከአዕራቦች) ወደ ኋላ ለቀሩት (እንዲህ) በላቸው: «የብርቱ ኃይል ባለቤት ወደ ሆኑ ህዝቦች ውጊያ ወደ ፊት ትጠራላችሁ፤ ትጋደሏቸዋላችሁ። ወይም ይሰልማሉ። ብትታዘዙም አላህ መልካም ምንዳን ይሰጣችኋል። ከአሁን በፊት እንደ ሸሻችሁ ብትሸሹ ደግሞ አሳማሚ ቅጣት ይቀጣችኋል።»

(ሰዎች ሆይ!) በአይነስውር ላይ (ከዘመቻ በመቅረቱ) ኃጢአት የለበትም። በአንካሳ ላይም ኃጢአት የለበትም። በበሽተኛም ላይ ኃጢአት የለበትም። አላህንና መልዕክተኛውን የሚታዘዝ ሁሉ ከስሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች ያስገባዋል። የሚያፈገፍገዉንም ሁሉ አሳማሚ ቅጣት ይቀጣዋል።

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከምዕመናኖቹ በዛፊቱ ስር ቃል ኪዳን በሚጋቡህ ጊዜ አላህ በእርግጥ ከእነርሱ ወደደ። በልቦቻቸዉም ውስጥ ያለውን ዐወቀ። በነሱም ላይ እርጋታን አወረደ። ቅርብ የሆነንም መክፈት መነዳቸው።

ብዙዎች የተማረኩትን ገንዘቦች የሚወስዷቸው የሆኑን መነዳቸው። አላህም ሁሉን አሸናፊና ጥበበኛ ነው።

(አማኞች ሆይ!) አላህ ብዙዎቹን ምርኮዎች የምትወስዷቸው የሆኑን አላህ ቃል ገባላችሁ። ይህንንም ለእናንተ አስቸኮለላችሁ። ከናንተም የሰዎችን እጆች ሠበሰበላችሁ። (ታመሰግኑ ዘንድ) ለአማኞችም ምልክት እንድትሆን ቀጥተኛውን መንገድ ይመራችሁም ዘንድ ይህን አደረግንላችሁ።

ሌላይቱንም በእርሷ ላይ ገና ያልቻላችኋትን አላህ ያወቃትን ለእናንተ አዘጋጅቷል። አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነውና።

እነዚያም የካዱት (የመካ ሰዎች) በተዋጓችሁ ኖሮ ለሽሽት ጀርባዎችን ባዞሩ ነበር። ከዚያ ዘመድም ረዳትም አያገኙም።

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ ያችን ከዚህ በፊት በእርግጥ ያለፈችውን ልማድ ደነገገ። ለአላህ ልማድ መቸም ለውጥን አታገኝም።

እርሱ(አላህ) ያ በመካ ውስጥ በእነርሱ ላይ ካስቻላችሁ በኋላ እጆቻቸዉን ከእናንተ ላይ እጆቻችሁንም ከእነርሱ ላይ የከለከለ ነው። አላህም የምትሰሩትን ነገር ሁሉ ተመልካች ነው።

እነርሱ ማለት እነዚያ በአላህ የካዱ፤ ከተከበረው መስጊድም የከለከሏችሁ መስዋዕትንም የታሰረ ሲሆን ወደ ስፍራው እንዳይደርስ የከለከሉ ናቸው። የማታውቋቸው ወንድ አማኞችና ሴት ምዕመናት ከከሓዲያኑ ጋር ባልነበሩ ኖሮና እናንተም ያለ እውቀት እነርሱን ረግጣችሁ ከእነርሱ (በኩል) መከፋት የሚነካችሁ ባይሆን ኖሮ እጆቻችሁን ባላገድን ነበር። አላህም የሚፈልገውን ሰው በእዝነቱ ውስጥ ያስገባ ዘንድ (እጆቻችሁን አገደ)። በተለዩ ኖሮ እነዚያን ከእነርሱ ውስጥ በአላህ የካዱትን አሳማሚን ቅጣት በቀጣናቸው ነበር።

እነዚያ በአላህ የካዱት ደራይቱን (እልህን) የመሀይምነቲቱን ደራ (እልህ) በልቦቻቸው ውስጥ ባደረጉ ጊዜ በቀጣናቸው ነበር። አላህም በመልዕክተኛው ላይ እና በምዕመናኖቹ ላይ እርጋታውን አወረደ። መጠበቂያይቱንም ቃል አስያዛቸው። በእርሷም ተገቢዎች ባለቤቶቿም ነበሩ። አላህም በነገሩ ሁሉ አዋቂ ነው።

ህልሙ እውነተኛ ሲሆን አላህ የፈለገ አንደሆነ ጸጥተኞች ሆናችሁ ራሳችሁን ላጭታችሁ አሳጥራችሁ የማትፈሩ ስትሆኑ የተከበረውን መስጊድ በእርግጥ ትገባላችሁ ያለውን ህልም አሏህ ለመልዕክተኛው(ለሙሀመድ) እውነት አደረገለት። (አላህም) (በእርቁ ውስጥ ያለውን ጥበብ) ያላወቃችሁትን ነገር አወቀ። እናም ከዚህ በፊት ቅርብን የመክፈት እርቅ አደረገ።

እርሱ (አላህ) ያ መልዕክተኛውን (ነብዩ ሙሐመድን) በመሪ መጽሐፍና በእውነተኛ ሃይማኖት በሃይማኖት ሁሉ ላይ ሊያልቀው (የበላይ ሊያደርገው) የላከ ነው። መስካሪነትም አላህ በቃ።

የአላህ መልዕክተኛ (ነብዩ) ሙሐመድ እና እነዚያም የእርሱ ጓደኞች በከሓዲያን ላይ ብርቱዎች በመካከላቸው ተዛዛኞች ናቸው። አጎንባሾች፤ ሰጋጆች፤ ሆነው ታያቸዋለህ። ችሮታንና ውዴታን ሁልጊዜም ከአላህ ይፈልጋሉ። ምልክታቸው ከስግደታቸው ፈለግ ስትሆን በፊታቸው ላይ ናት። ይህ በተውራት (የተነገረላቸው) ጸባያቸው ነው። በኢንጅል ውስጥ የተጠቀሰው ምሳሌያቸው ደግሞ ቀንዘሉን እንደ አወጣ አዝመራና (ቀንዘሉን) እንዳበረታው እንደ ወፍራምና ገበሬዎቹን የሚያስደነቅ ሆኖ አገዳዎቹ ላይ ተስተካክሎ እንደቆመ (አዝመራ) ነው። ያበረታቸውና ከሓዲያን በእርሱ ሊያሰቆጭ ነው። አላህ እነዚያን በእሱ ያመኑትንና ከእነርሱ በጎዎችን ተግባራት የሰሩትን ሁሉ ምህረትንና ታላቅ ምንዳን ቃል ገብቶላቸዋል።