عربيEnglish

The Noble Qur'an Encyclopedia

Towards providing reliable exegeses and translations of the meanings of the Noble Qur'an in the world languages

The moon [Al-Qamar] - Amharic Translation - Africa Academy

Surah The moon [Al-Qamar] Ayah 55 Location Maccah Number 54

የትንሳኤ ቀን ተቃረበ። ጨረቃም ተገመሰ።

ከሓዲያን ተዐምርን ቢያዩም እንቢ ብለው ይዞራሉ። «ይህ ዘውታሪ ድግምት ነው» ይላሉ።

አስተባበሉም ። ዝንባሌዎቻቸውንም ተከተሉ። ነገርም ሁሉ (ወሰን አለው) ረጊ ነው።

ከዜናዎቹ በእርሱ ውስጥ መገሰጫ የሚሆን ነገር ያለበት በእርግጥ መጣላቸው።

ሙሉ የሆነ ጥበብ (መጣላቸው)። ግን አስፈራሪዎች (ለማያምኑት) አይፈይዱም።

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከእነርሱም ተውና ዙር። (ይልቁንስ) ጠሪው መልዓክ ወደ አስደንጋጭ ነገር የሚጠራበትን ቀን አስታውስ።

ዓይኖቻቸው ያቀረቀሩ ሆነውና ፍጹም የተበተኑ አንበጣ መስለው ከየመቃብሮቻቸው ይወጣሉ።

ወደ ጠሪው አንገቶቻቸውን ሳቢዎችና ቸኳዮች ሆነው ይወጣሉ። ከሓዲያን ያን ጊዜ «ይህ ብርቱ ቀን ነው» ይላሉ።

ከእነርሱ በፊት የ(ነብዩ) ኑህ ህዝቦች አስተባበሉ። ባሪያችንንም ኑህን አስተባበሉ። «ዕብድ ነዉም» አሉት። ተገላመጠም።

ጌታውንም «እኔ የተሸነፍኩ ነኝና እርዳኝ» ሲል ተጣራ።

ወዲያውም የሰማይን ደጃፎች በሚንቧቧ ውሃ ከፈትን።

የምድርንም ምንጮች በሃይል አፈነዳን። የሰማዩና የምድሩ ውሃዉም ቀድሞ በተወሰነ ሁኔታ ላይ ተገናኘ።

ባለ ብዙ ሳንቃዎችና ባለ ብዙ ሚስማሮች በሆነችው ታንኳ ላይም ጫንነው።

በዓይኖቻችን እይታ (በጥበቃችን ስር) ሆና ትንሻለላለች። ተክዶ ለነበረ ሰው ምንዳ ይህን ሰራን።

ተዓምር አድርገንም በእርግጥ ተውናት። ተገሳጭ አለን?

ቅጣቴና ማስጠንቀቂያዎቼስ እንዴት ነበሩ?

ቁርኣንን ለመገንዘብ በእርግጥ አገራነው። ተገሳጭ አለን?

የዓድ ህዝቦች አስተባበሉ። ቅጣቴና ማስጠንቀቂያዎቼስ እንዴት ነበሩ?

እኛ በእነርሱ ላይ ዘወትር መናጢ በሆነ ቀን በኃይል የምትንሻሻ ነፋስን ላክንባቸው።

ሰዎችንም ልክ ከስሮቻቸው እንደተጎለሰሱ የዘንባባ ግንዶች መስለው ከየተደበቁበት ትነቅላቸዋለች።

ቅጣቴና ማስጠንቀቂያዎቼስ እንዴት ነበሩ?

ቁርኣንንም ለመገንዘብ በእርግጥ አገራነው። ተገሳጭ አለን?

የሰሙድ ህዝቦች በአስፈራሪዎቹ አስተባበሉ።

(እንዲህም) አሉ: «ከእኛ የሆነን አንድን ሰው እንከተለዋለን? እኛ ያ! ጊዜ በስህተትና በእብደት ውስጥ ነን» አሉ።

«ከእኛ መካከል በእርሱ ላይ ብቻ ማስገንዘቢያ ራዕይ ተጣለለትን? አይደለም እርሱ ውሸታም ኩሩ ነው» አሉ።

ውሸታሙ ኩሩው ማን እንደሆነ ነገ በእርግጥ ያውቃሉ።

እኛ ሴት ግመልን ለእነርሱ መፈተኛ ትሆን ዘንድ ላኪዎች ነን። ተጠባበቃቸዉም ታገስም።

ውሃዉም በመካከላቸው የተከፈለ መሆኑን ንገራቸው። ከውሃ የሆነ ፈንታ ሁሉ በየተራ የሚጣዱት ነው።

ጓደኛቸውንም ጠሩት። ወዲያዉም (ሰይፉን) ተቀበለ። ወጋትም።

ቅጣቴና ማስጠንቀቂያዎቼስ እንዴት ነበሩ?

እኛ በእነርሱ ላይ አንዲትን ጩኸት ላክንባቸው። ወዲያዉም ከበረት አጣሪ (አጥር) እንደ ተሰባበረ እርጋፊ ሆኑ።

ቁርኣንን ለመገንዘብ በእርግጥ አገራነው። ተገሳጭ አለን?

የ(ነብዩ) ሉጥ ህዝብ በአስፈራሪዎቹ አስተባበሉ።

እኛ በእነርሱ ላይ ጠጠርን ያዘለች ነፋስ ላክን። የሉጥ ቤተሰቦች ብቻ ሲቀሩ እነርሱንስ በሌሊት መጨረሻ ላይ አዳንናቸው።

ከእኛ በሆነ ጸጋ (አዳናቸው።) ልክ እንደዚሁ ያመሰገነን ሰው እንመነዳለን።

(ሉጥ) ብርቱ አያያዛችንን በእርግጥ አስጠነቀቃቸው። በማስጠንቀቂያዎቹም ተከራከሩ።

ከእንግዶቹም እንዲያስመቻቸው ደጋግመው ፈለጉት። ወዲያዉም ዓይኖቻቸውን አበስን። «ቅጣቴንና ማስጠንቀቂያዎቼን ቅመሱ» አልናቸው።

በማለዳም ዘወታሪ የሆነ ቅጣት በእርግጥ ማለደባቸው።

«ቅጣቴንና ማስጠንቀቂያዎቼን ቅመሱ» ተባሉ።

ቁርኣንንም ለመገንዘብ በእርግጥ አገራነው። ተገሳጭ አለን?

የፈርዖንን ቤተሰቦችም ማስጠንቀቂያዎች በእርግጥ መጧቸው።

በተዓምራታችንም በሁሏም አስተባበሉ። የብርቱ ቻይንም አቀጣጥ ቀጣናቸው።

የእናንተ ከሓዲያኖቻችሁ ከእነዚያ (ከተጠቀሱት ሕዝቦች) በላጮች ናቸውን? ወይስ ለእናንተ በመጽሐፎች ውስጥ በተለየ የተነገረ ነፃነት አላችሁ?

ወይስ «እኛ የተረዳን ክምቹዎች ነን» ይላሉ?

ክምቹዎቹ በእርግጥ ድል ይመታሉ። ጀርባዎቻቸውንም ያዞራሉ።

ይልቁንም ሰዓቲቱ ትንሳኤ ቀጠሯቸው ናት። ሰዓቲቱም በጣም የከበደችና የመረረች ናት።

አመጸኞች በስህተትና በእሳቶች ውስጥ ናቸው።

በእሳት ውስጥ በፊታቸው በሚጎተቱበት ቀን «የሰቀርን (የገሀነምን) መንካትን ቅመሱ» ይባላሉ።

ትዕዛዛችንም እንደ ዓይን ቅጽበት የሆነች አንዲት ቃል እንጂ ሌላ አይደለችም።

ብጤዎቻችሁንም በእርግጥ አጠፋን፤ ተገሳጭ አለን?

የሰሩትም ነገር ሁሉ በመጽሐፎች ውስጥ ነው።

ትንሹም ትልቁም ሁሉ የተፃፈ ነው።

አላህን ፈሪ የሆኑ ሰዎች ሁሉ በአትክልቶችና በወንዞች ውስጥ ናቸው።

እነርሱም (ውድቅ ቃልና መወንጀል በሌለበት) በእውነት መቀመጫ ውስጥ ቻይ ከሆነው ንጉስ (አላህ) ዘንድ ናቸው።