عربيEnglish

The Noble Qur'an Encyclopedia

Towards providing reliable exegeses and translations of the meanings of the Noble Qur'an in the world languages

The congregation, Friday [Al-Jumua] - Amharic Translation - Africa Academy

Surah The congregation, Friday [Al-Jumua] Ayah 11 Location Madanah Number 62

በሰማይና በምድር ውስጥ ያለው ሁሉ ንጉስ፤ ፍፁም (ከጉድለት ንጹህ)፤ አሸናፊና ጥበበኛ የሆነውን አላህን ያሞግሳል።

እርሱ ያ ለመሃይማን ዐረቦች የቁርአን አናቅጽን በእነርሱ ላይ የሚያነብላቸው፤ የሚያጠራቸዉም፤ መጽሐፍንና ጥበብን የሚያስተምራቸዉም የሆነን መልዕክተኛ ሙሐመድን ከእነርሱ መካከል የላከ ነው። እነርሱም ከእርሱ በፊት በግልጽ ስህተት ውስጥ ነበሩ።

ከነሱም ሌሎችም ገና ያልተከተሏቸው በሆኑት ላይ የላከው ነው። እርሱም አሸናፊና ጥበበኛ ነው።

ይህ የአላህ ችሮታ ነው። ለሚሻው ሰው ይሰጠዋል። አላህ የታላቅ ችሮታ ባለቤት ነው።

የእነዚያ ተውራትን የተጫኑትና ከዚያ ያልተሸከሟት (ያልሰሩባት) ሰዎች ምሳሌ ልክ መጽሐፎችን እንደሚሸከም አህያ ብጤ ነው። የእነዚያ በአላህ አናቅጽ ያስተባበሉት ህዝቦች ምሳሌ ከፋ። አላህም በዳዮችን ህዝቦች አይመራም።

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እናንተ አይሁዳውያን ሆይ! ከሰው ሁሉ በተለየ እኛ ብቻ ለአላህ ወዳጆች ነን ብትሉና በዚያ አባባላችሁ እውነተኞች እንደሆናችሁ እስቲ ሞትን ተመኙ» በላቸው።

እጆቻቸው ባስቀደሙት ኃጢአት ምክንያት በፍጹም አይመኙትም። አላህ በዳዮችን አዋቂ ነው።

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ያ ከእርሱ የምትሸሹት ሞት እርሱ በእርግጥ አግኚያችሁ ነው። ከዚያም ሩቁንና ቅርቡን አዋቂ ወደ ሆነው ጌታ በቂያማ ዕለት ተመላሾች ናችሁ። ትሰሩትም የነበራችሁትን ሁሉ ይነግራችኋል» በላቸው።

እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በአርብ (በጁሙዓ) ቀን ለሶላት ጥሪ በተደረገ ጊዜ ወደ አላህ ማውሳት (ኹጥባ፣ ሶላት) ተጣደፉ። መሸጥንም ተው። የምታውቁ ብትሆኑ ይህ ለእናንተ በጣም የተሻለ ነው።

ሶላቷ በተፈጸመችም ጊዜ በምድር ላይ ተበተኑና የአላህን ችሮታ ፈልጉ። ልትድኑ ይከጀላልና አላህንም በብዙው አውሱ።

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ንግድን ወይም ዛዛታን ባዩ ጊዜም ቆመህ የተውህ ሲሆኑ ወደ እርሷ ይበተናሉ። «አላህ ዘንድ ያለው ከዛዛታም ከንግድም በላጭ ነው። አላህም ከሰጭዎች ሁሉ ይበልጥ ሲሳይን ሰጪ ነው» በላቸው።