The Noble Qur'an Encyclopedia
Towards providing reliable exegeses and translations of the meanings of the Noble Qur'an in the world languagesThe Hypocrites [Al-Munafiqoon] - Amharic Translation - Africa Academy
Surah The Hypocrites [Al-Munafiqoon] Ayah 11 Location Madanah Number 63
አስመሳዮች በመጡህ (ወደ አንተ በመጡ) ጊዜ «አንተ የአላህ መልዕክተኛ መሆንህን በእርግጥ (ምለን) እንመሰክራለን» ይላሉ። አላህም አንተ በእርግጥ መልዕክተኛው መሆንህን ያውቃል። አላህም አስመሳዮችን ውሸታሞች መሆናቸውን ይመሰክራል።
መሓላዎቻቸውን ጋሻ አድርገው ያዙ። ከአላህም መንገድ ከለከሉ። እነርሱ ይሰሩት የነበሩት ነገር ሁሉ ከፋ።
ይህ እነርሱ (በምላስ) አምነው ከዚያም (በልብ) የካዱ በመሆናቸው በልቦቻቸዉም ላይ ታተመባቸው። ስለዚህ እነርሱ አያውቁም።
ባየሃቸው ጊዜ አካሎቻቸው ያስደንቁሃል። ቢናገሩም ንግግራቸውን ታዳምጣለህ። እነርሱ ልክ ወደ ግድግዳ የተጠጉ ግንዶችን ይመስላሉ። ጩኸትን ሁሉ በእነርሱ ላይ ነው ብለው ያስባሉ። እነርሱ ጠላቶች ናቸውና ተጠንቀቃቸው። አላህ ይጋደላቸው። (ከእምነት) እንዴት ይመለሳሉ (ያፈገፍጋሉ)።
ለእነርሱም፡- «ኑ የአላህ መልዕክተኛ ለእናንተ ምህረትን ይለምንላችኋል» በተባሉ ጊዜ በማፌዝ ራሶቻቸውን ያዞራሉ። እነርሱም ትዕቢተኞች ሆነው ሲሸሹ ታያቸዋለህ።
ምህረትን ብትለምንላቸውም ባትለምንላቸዉም በእነርሱ ላይ ሁሉም እኩል ነው። አላህ ለእነርሱ በፍጹም አይምርም። አላህ አመጸኛ ህዝቦችን አይመራምና።
እነርሱ፡- «እነዚያ ከአላህ መልዕክተኛ ዘንድ ያሉት ሰዎች እስከ ሚበታተኑ ድረስ ምጽዋት አትስጡ» የሚሉ ናቸው። የሰማያትና የምድር ድልቦች የአላህ ብቻ ናቸው። ግን አስመሳዮች አይገነዘቡም።
«ወደ መዲና ብንመለስ አሸናፊው ወራዳውን በእርግጥ ከእርሷ ያስወጣል» ይላሉ። አሸናፊነትም ለአላህ ለመልዕክተኛው እና ለምዕምናን ብቻ ነው። ግን አስመሳዮች አያውቁም።
እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ገንዘቦቻችሁና ልጆቻችሁ አላህን ከማስታወስ አያታልሏችሁ (አያዘናጓችሁ)። ይህንንም የሚሰሩ ሰዎች እነዚያ እነርሱ ከሳሪዎች ናቸው።
አንዳችሁም ሞት ሳይመጣበትና «ጌታየ ሆይ! እንድመጸውትና ከደጋጎችም ሰዎች እንድሆን ጥቂት ጊዜ ብታቆየኝ ኖሮ እመኛለሁ» ከማለቱ በፊት ከሰጠናችሁ ሲሳይ ለግሱ።
ማንኛይቱም ነፍስ የሞት ጊዜዋ በመጣባት ጊዜ አላህ በፍጹም አያቆያትም። አላህም በምትሰሩት ሁሉ ውስጠ አዋቂ ነው።

