عربيEnglish

The Noble Qur'an Encyclopedia

Towards providing reliable exegeses and translations of the meanings of the Noble Qur'an in the world languages

The enshrouded one [Al-Muzzammil] - Amharic Translation - Africa Academy

Surah The enshrouded one [Al-Muzzammil] Ayah 20 Location Maccah Number 73

አንተ ተከናናቢው ሆይ።

ሌሊቱን (ሁሉ) ጥቂት ሲቀር ቁም (ስገድ)።

ግማሹን (ቁም) ወይም ከእርሱ ጥቂትን ቀንስ።

ወይም በእርሱ ላይ ጨምር። ቁርኣንንም በዝግታ አንብብ።

እኛ ባንተ ላይ ከባድ ቃልን እናወርዳለንና።

ሌሊት መነሳት (ህዋሳትንና ልብን) ለማስማማት በጣም ብርቱ ነው። ለማንበብም ትክክለኛ ሰዓት ነው።

ላንተ በቀን ውስጥ ረዥም የመዘዋወርያ ሰዓት አለህ።

የጌታህን ስም አውሳ። ወደ እርሱም (አምልኮ) መቋረጥን ተቋረጥ።

(እርሱም) የምስራቅና የምዕራብ ጌታ ነው። ከእርሱ ሌላ ትክክለኛ አምላክ የለም። መጠጊያ አድርገህም ያዘው።

(ከሓዲያንም) በሚሉት ላይ ታገስ። መልካምንም መተው ተዋቸው።

የድሎት ባለቤቶችም ከሆኑት አስተባባዮች ጋር ተወኝ። ጥቂትንም ጊዜ አቆያቸው።

ከእኛ ዘንድ ከባድ ማሰሪያዎችና እሳት አሉንና።

(ጉሮሮን) የሚያንቅ ምግብና አሳማሚ ቅጣትም አለ።

በዚያ ምድርና ጋራዎች በሚርገፈገፉበት፤ ጋራዎችም ፈሳሽ የአሸዋ ክምር በሚሆኑበት ቀን።

እኛ ወደ ፈርዖን መልዕክተኛን እንደላክን ሁሉ በእናንተ ላይ መስካሪ መልዕክተኛንም ወደ እናንተ ላክን።

ፈርዖንም መልዕክተኛውን አመጸ። ብርቱ መያዝንም ያዝነው።

(በአላህ) ከካዳችሁ ያን ልጆችን ሸበቶዎች የሚያደርገውን ቀን ቅጣት እንዴት ትጠነቀቃላችሁ?

ሰማዩ በቀኑ ተሰንጣቂ ነው። ቀጠሮዉም ተፈፃሚ ነው።

ይህች መገሰጫ ናት። (መዳንን) የሻ (የፈለገ) ሰው ወደ ጌታው (የሚያደርሰዉን) መንገድ ይይዛል።

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አንተ ከሌሊቱ ሁለት ሶስተኛ እጅ ያነሰን፤ ግማሹንም ሲሶውንም የምትቆም መሆንህን ጌታህ ያውቃል። (ሙስሊሞች) ከእነዚያም አብረውህ ካሉ ከፊሎች የሚቆሙ መሆናቸውንም ያውቃል። አላህ ሌሊትና ቀንን ይለካል። (የሌሊቱን ሰዓታት) ልትቆጣጠሩት የማትችሉ መሆናችሁን አወቀ። እናም በእናንተ ላይ ህጉን ወደ ማቃለል ተመለሰላችሁ። ስለዚህ ከቁርኣን (በስግደት) የተቻላችሁን ያህል አንብቡ። ከናንተ ውስጥ በሽተኞች፤ ሌሎችም ከአላህ ችሮታ ለመፈለግ በምድር ላይ የሚጓዙ፤ ሌሎችም በአላህ መንገድ የሚጋደሉ እንደሚኖሩ አወቀ። (ስለዚህ አቃለለላችሁ)፤ ከእርሱ (ከቁርኣን) የቻላችሁትን አንብቡ። ሶላትንም ስገዱ። ዘካንም ስጡ። ለአላህ መልካም ብድርንም አበድሩ። ከመልካም ስራም ለነፍሶቻችሁ የምታስቀድሙትን ሁሉ የተሻለና በምንዳም ታላቅ ሆኖ በአላህ ዘንድ ታገኙታላችሁ። አላህን ምህረት ለምኑት። አላህ መሀሪና አዛኝ ነውና።