عربيEnglish

The Noble Qur'an Encyclopedia

Towards providing reliable exegeses and translations of the meanings of the Noble Qur'an in the world languages

The tidings [An-Naba] - Amharic Translation - Africa Academy

Surah The tidings [An-Naba] Ayah 40 Location Maccah Number 78

ከምን ነገር ይጠያየቃሉ?

ከታላቁ ዜና (ከትንሳኤና ከቁርኣን) ይጠያየቃሉ።

ስለዚያ እነርሱ በእርሱ ላይ ስለተለያዩበት (ስለተወዛገቡበት)።

ጉዳዩ እነርሱ እንደሚሉት አይደለም። (ትክክለኛውን) ወደ ፊት ያውቃሉ።

ከዚያም ይከልከሉ፤ (ትክክለኛውን) ወደ ፊት ያውቃሉ።

ምድርን ምንጣፍ አላደረግንምን?

ጋራዎችንም ችካሎች (አላደረግንምን)?

ጥንዶች አድርገንም ፈጠርናችሁ።

እንቅልፋችሁንም እረፍት አደረግን።

ሌሊቱንም ልባስ አደረግን።

ቀኑንም ለኑሮ መስሪያ (ለጉዳይ መከወኛ) አደረግን።

ከበላያችሁም ሰባት ብርቱዎችን (ሰማያት) ገነባን።

አንጸባራቂ ብርሃንንም አደረግንላችሁ።

ከአረገዙት ደመናዎችም የሚንቧቧ ውሃን አወረድን።

በእርሱ እህልንና ቅጠላ ቅጠልን፤ እናወጣ ዘንድ(አወረድን)።

የተቆላለፉ አትክልቶችንም ።

(በህዝቦች መካከልም) የመለያው ቀን የተወሰነ ጊዜ ነው።

(ይሀዉም) በቀንዱ በሚነፋበትና በቡድን በቡድን ሆናችሁም በምትመጡበት ቀን ነው።

ሰማይም በምትከፈትና ባለ ብዙ ደጃፎችም በምትሆንበት ቀን፤

ጋራዎችም ከቦታቸው በሚኼዱበትና እንደ ሲሪብዶም በሚሆኑበትም ቀን ነው።

ገሀነም (ለከሓዲያን) መጠባበቂያ ኬላ (ስፍራ) ናት።

ለህግ ተላላፊዎች መመለሻ ስትሆን።

በውስጧ ብዙ ዘመናትን ነዋሪዎች ሲሆኑ፤

በውስጧ ቅዝቃዜንም መጠጥንም አይቀምሱም (አያገኙም)።

ሙቅ የፈላ ውሃንና እዥን እንጂ

ተመጣጣኝን ምንዳ ይመነዳሉ።

ምርመራ (እንዳለባቸው) አይጠብቁም ነበርና።

በአናቅጻችንም ማስተባበልን አስተባበሉ።

ነገሩን ሁሉ የተፃፈ ሲሆን አጠቃለልነው።

«(የጃችሁን) ቅመሱም፤ ቅጣትን እንጂ ሌላን አንጨምርላችሁም» (ይባላሉም)።

ለጥንቁቆቹ (አላህን ለሚፈሩ) ስኬት አላቸው።

አትክልቶችና ወይኖችም፤

በእድሜ እኩያዎች የሆኑ ጡተ ጉችማዎችም፤

የተሞሉ ብርጭቆዎችም፤

በውስጧ ትርፍ ቃልንም፤ ማስዋሸትንም አይሰሙም።

ከጌታህ የሆነን ምንዳ፤ በቂ ስጦታን ተሰጡ።

የሰማያትና የምድር በመካከላቸዉም ላለው ሁሉ ጌታ ከሆነውና በጣም አዛኝ ከሆነው ተመነዱ፤ ከእርሱ ጋር መነጋገርን አይችሉም።

መልአኩ (ጅብሪል) እና ሌሎች መላዕክትም የተሰለፉ ሆነው በሚቆሙበት ቀን አርረህማን ለእርሱ የፈቀደለትና ትክክለኛን ቃል ያለ ብቻ ቢሆን እንጂ መነጋገርን አይችሉም።

ያ! የእውነት ቀን ነው። የፈለገ ሰው ወደ ጌታው በመልካም ተግባር መመለስን ተግባሩ አድርጎ ይይዛል።

እኛ ቅርብ የሆነን ቅጣት አስጠነቀቅናችሁ። ሰው ሁሉ በሁለት እጆቹ ያስቀደመውን የሚያይበትና ከሓዲያን ሁሉ «ዋ ምኞቴ! ምንነው አፈር በሆንኩ (ባልተቀሰቀስኩኝ)» የሚሉበት ቀን።