The Noble Qur'an Encyclopedia
Towards providing reliable exegeses and translations of the meanings of the Noble Qur'an in the world languagesHe Frowned [Abasa] - Amharic Translation - Africa Academy
Surah He Frowned [Abasa] Ayah 42 Location Maccah Number 80
ፊቱን አጨፈገገ፤ ዞረም፤
ዓይነስውሩ ወደ እርሱ ስለመጣ።
(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ምን ያሳውቅሃል? ምን አልባትም (ይህ አይነስውር ሰው ካንተ በሚሰማው ምክር ከኃጢአቶቹ) ሊጥራራ ይከጀላል።
ወይም ሊገሰጽና ግሳጼይቱም ልትጠቅመው ይከጀላል።
ያ! (በገንዘቡ) የተብቃቃውን ሰውማ፤
አንተ ለእርሱ ትዘጋጃለህ።
ባይጥራራ (ባያምን)፤ ባንተ ላይ ምንም የሌለብህ ስትሆን፤
ያ! እየገሰገሰ ወደ አንተ የመጣው ሰውማ፤
እርሱ አላህን የሚፈራ ሲሆን፤
አንተ ከእርሱ ትዘናጋለህ።
ተከልከል፤ (ቁርኣን) ማስገንዘቢያ ነው።
የፈለገ ሰው ሁሉ (ቁርኣኑን) ያስታውሰዋል።
በተከበሩት ጹሑፎች ውስጥ ነው።
ከፍ በተደረገች፤ ንጹህም በተደረገች (ጹሑፎች ውስጥ ነው)።
በጸሐፊዎች መላዕክት እጆች (ንጹህ የተደረገ)።
የተከበሩና ታዛዦች በሆኑት ጸሐፊዎች (እጆች)፤
ሰው ተረገመ። ምን ከሓዲ አደረገው?
(ጌታው) ከምን ነገር ፈጠረው?
(አያስብምን?) ከፍትወት ጠብታ ፈጠረው፤ መጠነዉም።
ከዚያም (መውጫ) መንገዱን አገራለት።
ከዚያም ገደለው። እንዲቀበርም አደረገው፤
ከዚያ ማንሳቱን በፈለገ ጊዜ ያስነሳዋል።
በእውነት ያንን ጌታው ያዘዘውን ገና አልፈጸመም።
ሰው ወደ ምግቡ ይመልከት፤
እኛ ውሃን ማንቧቧትን ያንቧቧን መሆናችንን፤
ከዚያ ምድርን (በቡቃያ) መሰንጠቅን የሰነጠቅን፤
በውስጧም እህልን ያበቀልን
ወይንንም እርጥብ ሳርንም፤
የዘይት ወይራንም ዘንባባንም፤
ጭፍቆች አትክልቶችንም፤
ፍራፍሬንና፤ የከብት መኖንም (ያበቀልን መሆናችንን ይመልከት)።
ለእናንተም ለእንሰሶቻችሁም መጠቀሚያ ይሆን ዘንድ (ይህን ሰራን)።
አደንቋሪይቱ (መከራ) በመጣች ጊዜ፤
ሰው ከወንድሙ በሚሸሽበት ቀን፤
ከእናቱም፤ ከአባቱም፤ (በሚሸሽበት ቀን)
ከሚስቱና ከልጆቹም፤ (በሚሸሽበት ቀን)
ከእነርሱ ለየሰው ሁሉ በዚያ ቀን ከሌላው የሚያብቃቃው ሁኔታ አለው።
ፊቶች በዚያ ቀን አብሪዎች፤
ሳቂዎችና ተደሳቾች ናቸው።
ፊቶች ደግሞ በዚያ ቀን በላያቸው ላይ ትብያ አለባቸው።
ጥቁረት ትሸፍናቸዋለች፤
እነዚያ እነርሱ በአላህ ከሓዲያን እና በትዕዛዙ ላይ አመጸኞቹ ናቸው።

