The Noble Qur'an Encyclopedia
Towards providing reliable exegeses and translations of the meanings of the Noble Qur'an in the world languagesThe morning star [At-Tariq] - Amharic Translation - Africa Academy
Surah The morning star [At-Tariq] Ayah 17 Location Maccah Number 86
በሰማዩ እና ሌሊት በሚመጣውም እምላለሁ።
(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የሌሊት መጪው ምን እንደሆነ ምን አሳወቀህ?
ጨለማውን ሰንጣቂ ኮከብ ነው።
ነፍስ ሁሉ በእርሷ ላይ ጠባቂ ያለባት እንጂ ሌላ አይደለችም።
የሰው ልጅ ከምን እንደተፈጠረ ይመልከት፤
ከተስፈንጣሪ ውሃ (የዘር ፈሳሽ) ተፈጠረ።
ከጀርባና ከእርግብግቢቶች መካከል የሚወጣ ከሆነ የዘር ፈሳሽ ውሃ (ተፈጠረ)።
አላህ እርሱን በመመለሱ ላይ በእርግጥ ቻይ ነው።
ሚስጥሮች በሚገለጹበት ቀን፤
(ለሰው) ምንም ኃይልና ረዳት አይኖረዉም።
የመመለስ ባለቤት (ዝናባማ) በሆነችው ሰማይ እምላለሁ።
(በበቃይ) የመሰንጠቅ ባለቤት በሆነችው ምድርም እምላለሁ።
እርሱ (ቁርኣን)፤ (እውነትን ከውሸት) የሚለይ (የአላህ) ቃል ነው።
እርሱም ቀልድ አይደለም።
እነርሱ በእርግጥ ተንኮልን ያሴራሉ (ይሸርባሉ)።
እኔም (ለእነርሱ) ዘዴን እዶልታለሁ (አዘጋጃለሁ)።
(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከሓዲያንን ቀን ስጣቸው። ጥቂትን ጊዜ አቆያቸው (ታገሳቸው)።

