عربيEnglish

The Noble Qur'an Encyclopedia

Towards providing reliable exegeses and translations of the meanings of the Noble Qur'an in the world languages

The Overwhelming [Al-Ghashiya] - Amharic Translation - Africa Academy

Surah The Overwhelming [Al-Ghashiya] Ayah 26 Location Maccah Number 88

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የሸፋኝቱ ትንሳኤ ወሬ መጣልህን?

በዚያ ቀን (የከሓዲያን) ፊቶች ተዋራጆች ናቸው።

ሰሪዎች ለፊዎች ናቸው።

የምታቃጥልን እሳት ይገባሉ።

በጣም ከፈላች ምንጭም ይጋታሉ።

ዶሪዕ ከሚባል (እሾሃማ) ዛፍ እንጂ ሌላ ምግብ የላቸዉም።

አካልን አያሰባ፤ ከረኃብም አያብቃቃ፤

(የአማንያን) ፊቶች በዚያ ቀን ተቀማጣዮች ናቸው።

በስራቸውም ተደሳቾች ናቸው።

በከፍተኛ ገነት ውስጥ ናቸው።

በውስጧ ውድቅን ነገር አይሰሙም።

በውስጧ ፈሳሾች ምንጮች አሉ።

በውስጧ ከፍ የተደረጉ አልጋዎች አሉ።

በተርታ የተኖሩ ኩባያዎችም፤

የተደረደሩ መከዳዎችም፤

የተነጠፉ ስጋጃዎችም (አሉ)።

(ከሓዲያን) ግመል እንዴት እንደተፈጠረች አይመለከቱምን?

ሰማይም እንዴት ከፍ እንደተደረገች!

ተራራዎችም እንዴት እንደ ተቸከሉ!

ምድርም እንዴት እንደተዘረጋች አይመለከቱምን?!

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አስታውስም። አንተ አስታዋሽ ብቻ ነህና።

በእነርሱ ላይ አስገዳጅ (ተሿሚ) አይደለህም፤

ግን ከእውነት የዞረና የካደ፤

መመለሻቸው ወደ እኛ ብቻ ነው።

ከዚያም ምርመራቸው በእርግጥ በእኛ ላይ ብቻ ነው።