عربيEnglish

The Noble Qur'an Encyclopedia

Towards providing reliable exegeses and translations of the meanings of the Noble Qur'an in the world languages

The night [Al-Lail] - Amharic Translation - Africa Academy

Surah The night [Al-Lail] Ayah 21 Location Maccah Number 92

በሌሊቱ (በጨለማው) በሚሸፍነው ጊዜ፤ (እምላለሁ)።

ወንድንና ሴትን በፈጠረዉም (አምላክ) እምላለሁ።

ስራችሁ በእርግጥ የተለያየ ነው።

ያ! የሰጠና ጌታውንም የፈራማ፤

በመልካሚቱ (እምነትም) ያረጋገጠ ሰው

ያ! የሰሰተ በራሱም የተብቃቃ፤

በመልካሚቱም ያስተባበለውማ

(ወደ ገሀነም) በወደቀ ጊዜ ያ! ገንዘቡ ከእርሱ ምንም አይጠቅመዉም።

ቅኑን መንገድ መግለጽ በእኛ ላይ አለብን።

መጨረሻይቱም መጀመሪያይቱም ዓለም የእኛው ነው።

የምትንቀለቀል እሳት አስጠነቀቅኳችሁ።

ከእጅግ እድለ ቢሱ በስተቀር የማይገባባትን

ያ ያስተባበለና ከትዕዛዝም የሸሸ እድለ ቢስ (ነው የሚገባባት)።

አላህን በጣም ፈሪ የሆነ በእርግጥ ይርቃታል።

ያ (ከወንጀል) የሚጥራራ ሲሆን ገንዘቡን የሚለግስ፤

ለአንድም ሰው በእርሱ ዘንድ ተመላሽ የሚሆን ውለታ ሳይኖርበት።

ከሁሉ በላይ የሆነውን የጌታውን ፊት (ውዴታ) በመፈለግ ብቻ (ይህንን የሰራ) ሲቀር።

እርሱማ ወደ ፊት (በሚሰጠው) በእርግጥ ይደሰታል።