The Noble Qur'an Encyclopedia
Towards providing reliable exegeses and translations of the meanings of the Noble Qur'an in the world languagesThe morning hours [Ad-Dhuha] - Amharic Translation - Africa Academy
Surah The morning hours [Ad-Dhuha] Ayah 11 Location Maccah Number 93
በረፋዱም፤ (እምላለሁ)
በሌሊትም ጸጥ ባለ ጊዜ እምላለሁ።
(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህ አላሰናበተህም፤ አልጠላህምም።
የመጨረሻይቱ ዓለም ከመጀመሪያይቱም ይልቅ ላንተ በላጭ ናት።
ጌታህም ወደ ፊት (ብዙ ስጦታ) በእርግጥ ይሰጥሃል። ትደሰታለህም።
የቲም ሆነህ አላገኘህምና አላስጠጋህምን? (አስጠግቶሃል)።
(የሸሪዓን ሕግጋት) የማታውቅ ሆነህ አገኘህና መራህ።
ደሃም ሆነህ አገኘህና አበለጸገህ።
እናም የቲምን አትጨቁን።
ለማኝንም አትገላምጥ።
የጌታህንም ጸጋ ግለጽ።

