The Noble Qur'an Encyclopedia
Towards providing reliable exegeses and translations of the meanings of the Noble Qur'an in the world languagesSolace [Al-Inshirah] - Amharic Translation - Africa Academy
Surah Solace [Al-Inshirah] Ayah 8 Location Maccah Number 94
(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ልብህን ላንተ አላሰፋንልህም?
ሸክምህንም አላወረድንልህምን?
ያንን ጀርባህን ያከበደውን (ሸክም)
መወሳትህንም ከፍ አላደረግንልህ?
እናም ከችግር ጋር በእርግጥ ምቾት አለ።
ከችግር ጋር በእርግጥ ምቾት አለ።
(የጀመርከውን ጥሩ ስራ) በጨረስክ ጊዜ ወደ ሌላ ጥሩ ስራ ቀጥል (አስከትል)።
ክጃሎትህንም ወደ ጌታህ ብቻ አድርግ።

