عربيEnglish

The Noble Qur'an Encyclopedia

Towards providing reliable exegeses and translations of the meanings of the Noble Qur'an in the world languages

The Fig [At-Tin] - Amharic Translation - Africa Academy

Surah The Fig [At-Tin] Ayah 8 Location Maccah Number 95

በበለስና፤ በወይራ ዛፍ እምላለሁ፣

በሲና ተራራም፤

በዚህ በጸጥተኛው (ጸጥታ በነገሰበት) አገር (መካም) እምላለሁ።

በርግጥ ሰውን በጣም በአማረ አቋም ላይ ፈጠርነው።

ከዚያም (ከፊሉን) ከበታቾች ሁሉ በታች አድርገን መለስነው።

እነዚያ በአላህ ያመኑትና መልካም ተግባራት የሰሩት ሲቀሩ ለእነርሱማ የማይቋረጥ ምንዳ አለላቸው።

(የሰው ልጅ ሆይ) ታዲያ ከዚህ (እውነታ) በኋላ በፍርዱ ምን አስተባባይ አደረገህ?

አላህ ከፈራጆች ሁሉ ይበልጥ ፈራጅ አይደለምን?