The Noble Qur'an Encyclopedia
Towards providing reliable exegeses and translations of the meanings of the Noble Qur'an in the world languagesThe Clear proof [Al-Bayyina] - Amharic Translation - Africa Academy
Surah The Clear proof [Al-Bayyina] Ayah 8 Location Madanah Number 98
ከመጽሐፍ ባለቤቶችና ከአጋሪዎች እነዚያ በአላህ የካዱት ሰዎች ግልጽ አስረጂ እስኪመጣላቸው ድረስ (ከነበሩበት አቋም) ተወጋጆች አልነበሩም።
(አስረጂውም) የተጥራሩ (መጽሐፎችን) የሚያነብ ከአላህ የሆነ መልዕክተኛ ነው።
በውስጧም ቀጥተኛ የሆኑ ጹሁፎች አሉ።
እነዚያ መጽሐፉን የተሰጡ ሰዎችም ግልጽ አስረጂ ከመጣላቸው በኋላ እንጂ አልተለያዩም።
ሃይማኖትን ለአላህ ብቻ አጥሪዎችና ቀጥተኞች ሆነው አላህን ሊገዙት፤ ሶላትንም አስተካክለው ሊሰግዱ፤ ዘካንም በትክክል ሊሰጡ እንጂ ያልታዘዙ ሲሆን (ተለያዩ።) የቀጥተኛይቱ ሃይማኖት ድንጋጌም ይሀው ነው።
ከመጽሐፉ ባለቤቶችና ከአጋሪዎች እነዚያ የካዱት በውስጧ ዘውታሪዎች በሚሆኑባት የገሀነም እሳት ውስጥ ናቸው። እነዚያ ከፍጥረቱ ሁሉ መጥፎዎቹ እነርሱ ናቸው።
እነዚያ በትክክል አምነው በጎ ተግባራትንም የሰሩት እነዚያ ከፍጥረት ሁሉ በላጭ (ምርጦች) የሆኑት እነርሱ ናቸው።
ምንዳቸውም በስሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው ከጌታቸው ዘንድ የሚቸሯቸው የመኖሪያ ገነቶች ናቸው። በውስጣቸው ለዘልዓለም ዘውታሪዎች ሲሆኑ ይገቡባቸዋል። አላህ ከእነርሱ ወደደላቸው። እነርሱም ከእርሱ (ምንዳውን) ወደዱ። ይህ እድል ጌታውን ለፈራ ሁሉ ነው።

