عربيEnglish

The Noble Qur'an Encyclopedia

Towards providing reliable exegeses and translations of the meanings of the Noble Qur'an in the world languages

The earthquake [Al-Zalzala] - Amharic Translation - Africa Academy

Surah The earthquake [Al-Zalzala] Ayah 8 Location Madanah Number 99

(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ምድር በኃይል መንቀጥቀጧን በተንቀጠቀጠች ጊዜ፤

ምድርም ሸክሞቿን ባወጣች ጊዜ፤

ሰዉም "ምን ሆነች?" ባለ ጊዜ፤

በዚያ ቀን ወሬዎቿን ትናገራለች።

ጌታህ ለእርሷ አሳውቋታልና፤

በዚያ ቀን ሰዎች ሁሉ ስራዎቻቸውን እንዲያዩ ይደረጉ ዘንድ (እንደየስራቸው) የተበታተኑ ሆነው (ከየመቃብራቸው ወደ መቆሚያው ስፍራ) ይመለሳሉ።

የብናኝን ክብደት ያህል መልካም የሰራ ሰው ያገኘዋል።

የብናኝን ክብደት ያህል ክፋት የሰራ ሰውም ያገኘዋል።